news

¾›=ƒÄÉÁ ›W]ዎች ôÅ_i”

 

     ፈጣንና ሰፊ የሆነ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት የአሠሪው ባለሀብት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እየደገ መጥቷል፡፡ አሠሪዎች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ሰፊ የሥራ እድል የሚፈጥሩና ለመንግስት ከፍተኛ ግብር በማሳካት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መሠረተ ልማቶች እንዲስፋፉ የሚያደርጉ ዋነኛ የልማት ኃይል ናቸዉ፡፡ ስለሆነም የአደጉ አገራት ደረጃ ለመድረስና የበለፀገች ኢትዮÉያን እዉን ለማድረግ የአሠሪው ባለሀብት ሚና የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

    ¾ኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን የአሠሪው ባለሀብት ሁለንተናዊ ተሳትፎ የበለጠ ተጠናከሮ እንዲቀጥልና ድህነትን ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብ የአሠሪው አስተዋጽኦ የላቀ እንዲሆነ አሠሪው ባለሀብት ከተለያዩ ችግሮችና ተፅ©ኖዎች ነፃ ሆኖ ኃይሉንና ትኩረቱን የልማት ግንባታ ላይ ብቻ ማተኮር ያስፈልገዋል የሚል እምነት አለው፡፡ በመሆኑም የኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን የአሠሪው ባለሀብት መብት ከማስከበር እና ጥቅሙን ከማስጠበቅ አንፃር በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

 

    አሠሪዎች እንደየዘርፋቸው እንዲደራጁና የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንዲቻል በርካታ ተቋማትና ማህበራት እንዲደራጁ ተደርጓል@ እየተደረገም ነው፡፡ በዚህም ፌደሬሽኑ ተደራሽነቱን እያሰፋ የአባላት ቁጥርን እየጨመረ መጥቷል፡፡

 

    ይሁን እንጂ ይህ በ©ድሜው ቀደምት የሆነ የኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን የ©ድሜውን ያህል ጠንካራና የአሠሪው አለኝታ እንዲሆን የተሻለ አደረጃጀት ሊኖረው ይገባል፡፡ በመሆኑም የኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ በርካታ ችግሮችን ሊቀርፍና የሚችል ጠንካራ መዋቀራዊ አደረጃጀት እንዲኖር የኢትዮÉያ አሠሪዎች ኮንፌደሬሽን መመስረት እንዳለበት ውሳኔ ላይ ተደርሳóል፡፡

 

   በመሆኑም የአትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን የኢትዮጽያ አሠዎች ፌደሬሽን በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አሠሪ ባለሀብቶች ማለትም በትራንስፖርትና መገናኛ፣ በመኪና መገጣጠምና አስመጪነት፣ በግል ጤና ተቋማት ዘርፍ በሆሰፒታል በክሊኒክ በፋርማሲ፣ በቡና አምራችና ላኪነት፣ በኮንስትራክሽን በእርሻና አግሮ ኢንዱስትሪ፣ በምግብና መጠጥ አምራችነት፣ በብረታ ብረትና ቆርቆሮ አምራችነት፣ በሲሚንቶና ሲሚንቶ ውጤቶች፣ የቤትና የቢሮ እቃዎች፣ የባንክና ኢንሹራንስ አገልግሎት፣ በኃይል ማመንጨት ዘርፍ፣ በአበባና አትክልት፣ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፣ በተለያዩ ጅምላና ችርቻሮ አገልግሎት፣ በአስመጪና ላኪ እንዲሁም ቁጥራቸዉ በርካታ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮችና ሌሎች ዘርፎች በማህበርም ሆነ በተናጠል የተደራጁትን በአባልነት አቅፋል፡፡ አገር አቀፍ ሆቴሎችና መሰል አገልግሎት ሰጪ ማህበር እና ሀገር አቀፍ ጥቅቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርኘራይዝ ማህበር በጋራ የኢትዮÉያ አሠሪዎች ኮንፌደሬሽንን ለመመስረት የተለያዩ የቅድመ ሁኔታ ተግባራት እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የቅድመ ሁኔታ ተግባራት አንዱ የሆነው ሁለቱን አገር አቀፍ ማህበራት ማለትም አገር አቀፍ ሆቴሎችና መሰል አገልግሎት ሰጪ ማህበር ይህ ማህበር አንጋፋና ሌሎች አገር አቀፍ ማህበራት እንዲደራጁ መነሻ የሆነ ባለውለታ@ ለኢንዱስትሪ ማደግ፣ ለልማት መፋጠን፣ ለቱሪዝም መስፋፋት እና ለገፅታ ግንባታ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ያለ ግዙፍ የልማት ዘርፍ ነው፡፡

 

    አገር አቀፍ ጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርኘራይዝ ማህበር አወንታዊ አሸናፊነት፣ ተወዳዳሪነትና ሥራ ፈጣሪነትን በህብረተሰቡ አስተሳስብ ውስጥ እንዲሠርፅ በማድረግ የአገር የኢኮኖሚ መዋቅር ከዝቅተኛ ወደ ከፍተኛ ምርታማነትና ትርፋማነት እያደገ እንዲመጣ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ያለ ዝርፍ ነው፡፡

 

    ዘርፎቹ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸዉ በርካታ አሠሪዎች ባለሀብቶችና ሠራተኛን ያቀፉ፣ አያሌ ቁጥር ላላቸዉ ዜጐች የሥራ እድል የፈጠሩና ባለው የልማት እንቅስቃሴ ጉልህ ድርሻ ያላቸዉ ዘርፎች ናቸዉ፡፡

 

    ይሁን እንጂ አሠሪው ባለሀብት በርካታ ችግሮችን የሚጋፈጥባቸው ዘርፎችም ጭምር ናቸው፡፡ ስለሆነም የተሻለ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠር ለአሠሪው ባለሀብት የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች በተሻለ አፈፃፀም ለመሥራትና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት እንዲቻል ሁለንተናዊ አቅማቸውን በማሳደግ ወደ ፌደሬሽን መቀየሩ አስፈላጊ ነው፡፡

 

    በመሆኑም በጠቅላላ ጉባኤው መሠረት ኮንፌደሬሽን ለመመስረት እንዲቻል ሁለቱ አገር አቀፍ ማህበራትን ወደ ፌደሬሽን የመቀየር ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

 

¾ኮንôÅ_i” መመስረት አስፈላጊነት

        በአሁኑ ሰዓት አገራችን ውስጥ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ በመሆኑ የአሠሪዎች አስተዋጽኦ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የሚያስፈልጋቸዉ

የአገልግሎት አይነቶችም በዚሁ ልክ እያደገ መጥቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መፍትሔ የሚያሻቸው ለአሠሪው እንቅፋት የሆኑ በርካታ ችግሮችም እየጨመሩ ይገኛሉ፡፡

 

   በመሆኑም ችግሮችን በወቅቱ እየፈታ ግባችንን ለማሳካት እንዲቻል ጠንካራ መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥና የአፈፃፀም ብቃት እንዲኖር፣ ጠንካራ የአለም አቀፍ ግንኙነት ያለው፣ የተሟላ የሰለጠነ የሰው ኃይል ያካተተና በአጠቃላይ የአሠሪው ድምጽ ተሰሚነት ከፍ እንዲል በማድረግ የአሠሪውን ፍላጐት የሚያሟላ የአሠሪው አለኝታ የሆነ ኮንፌደሬሽን መመሥረት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

¾ኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ለሥራ አመራሮች ስልጠና ሰጠ

 

     የኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ለአሠሪው ባለሀብት በርካታ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህ በያዝነው የግንቦት ወር በኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ሐረር እና ትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለሚገኙ አሠሪ ባለሀብቶች ስለ ጥሩ የሥራ አመራር ባህሪያትና መገለጫዎች እንዲሁም አሠሪና ሠራተኛ አዋጅን በተመለከተ ስልጠና ሰጠ፡፡

 

    በሐረር ከተማ ከግንቦት 6-7/2008 ዓ.ም. የተሰጠውን ስልጠና በንግግር የከፈቱት የተከበሩ የሰላም አምባሳደር አቶ ታደለ ይመር የኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ኘሬዝዳንት እንደገለፁት አሠሪው ባለሀብት ከሠራተኛው ጋር መልካም ግንኙነትን በማዳበር ሙሉ ትኩረቱን ሥራን በመምራት ላይ በማተኮር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይኖርበታል፡፡ የኢንዱስትሪው ስኬትም ሆነ ውድቀት የሚወስነው አሠሪው በመሆኑ ዘመኑ የሚጠይቀውን የሥራ አመራር እውቀትና ክህሎት ሊኖረው ይገባል ብለዋል፡፡

 

    አክለውም እንደገለፁት የአሠሪው ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዲጐለብትና ለአገር እድገት የሚያደርገው አስተዋጽኦ የበለጠ እንዲጨምር ሁሉም አሠሪ ባለሀብት በየዘርፉ መደራጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

 

    በመቀጠልም ኘሬዝዳንቱ ጥሩ የሥራ መሪ መገለጫዎች በሚል ር©ስ ላይ ሥራን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችሉ የሥራ አመራር ባህሪያት በተመለከተ ሰፊ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም የአሠሪና ሠራተኛን አዋጅ አስመልክቶ አሠሪዎች ከሠራተኞች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ምን እንደሚመስል፣ ችግሮች እን¬ት መፈታት እንደሚቻልና ኃይልንና ትኩረትን ሥራ ላይ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን መጨመር በሚቻልበት ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

 

   በመጨረሻም የኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ሐረር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአባላትን ቁጥር ከመጨመርና ለአሠሪ ባለሀብት የተሻለ አገልግሎት ከመስጠት

 

 

 

አንፃር ከሌሎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተሻለ በመሆኑ ይህን አጠናክሮ የበለጠ እንዲተጋ ማሳሰቢያ በመስጠት ስልጠናውን አጠናቀዋል፡፡

 

   ከግንቦት 9-10/2008 ዓ.ም. በጥሩ የሥራ አመራር ባህሪያትና የሠራተኛና አሠሪ አዋጅን በተመለከተ ለኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ትግራይ ቅርንጫፍ ለአሠሪ ባለሀብቶች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠና የተሰጠው በተመሳሳይ ር©ሰ ጉዳዮች ሲሆን ከሐረር ቅርንጫፍ የተገኘውን ልምድና ተሞክሮ ለማሰራት እንዲቻል የሐረር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኘሬዝዳንት በስልጠናው በመገኘት ልምዳቸውን ለእህት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አካፍለዋል፡፡

 

   በተጨማሪም የትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን በተለያዩ የግባአት አቅርቦቶች ለማጠናከር እንዲቻል በኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን  አማካይነት ከአለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) በእርዳታ የተገኙትን ግባአቶች አቶ ታደለ ይመር የኢትዮÉያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ኘሬዝዳንት ለትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኘሬዝዳንት አስረክበዋል፡፡ አክለውም ያለውን ጅምር እንቅስቃሴ የበለጠ በማጠናከር ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ጠንካራና የአሠሪዎች ድምጽ መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

   ስልጠናውን የተከታተሉ በርካታ የድርጅት ባለቤቶችና አሠሪ ባለሀብቶች በተሰጣቸው የሥራ አመራር ስልጠና መደሰታቸውንና ሥራቸውን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል ትልቅ ግባ©ት እንዳገኙ ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል፡፡

News

  የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌደሬሽን        ፈጣንና ሰፊ የሆነ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት የአሠሪው ባለሀብት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እየደገ መጥቷል፡፡ አሠሪዎች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ሰፊ የሥራ እድል...
¾›=ƒÄÉÁ ›W]ዎች ôÅ_i”        ፈጣንና ሰፊ የሆነ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት የአሠሪው ባለሀብት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እየደገ መጥቷል፡፡ አሠሪዎች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ሰፊ የሥራ እድል...
  The Ethiopian Employers Federation in collaboration with ILO has conducted a one day training program at Capital Hotel, in Addis Ababa.  The training...
The Ethiopian Employer’s Federation is the voice of employers and its major objective is to safeguard the right and benefit of employers. It is also...
The Ethiopian Employers’ Federation celebrated its 62 establishment and the 18th years anniversary of reestablishment by the theme of “Employers’ are...

Membership

  • Benefits of EEF Membership

    EEF, as the apex employers' organization in the Nation, works in the best interest of all the private sector on national, regional and international level. EEF offers a wide array of benefits to its members all designed to improve workplace relations, increase productivity, and to create enabling business environment.

    Read more...

Gallery

http://eef-ethiopia.org/modules/mod_image_show_gk4/cache/phocagallery.image1gk-is-97.jpglink
http://eef-ethiopia.org/modules/mod_image_show_gk4/cache/N1gk-is-97.JPGlink
http://eef-ethiopia.org/modules/mod_image_show_gk4/cache/N2gk-is-97.JPGlink
http://eef-ethiopia.org/modules/mod_image_show_gk4/cache/image5gk-is-97.jpglink
«
»
Loading…

Please enter youtube id.